ስታርተር
ከደብተር ላለፈ አንድ ሱቅ
እንነጋገር
- የሽያጭ ማሳያና የሽያጭ መዝገብ
- ክምችት ከምርት ዓይነቶች ጋር
- አንድ ቅርንጫፍ፣ ጥቂት ተጠቃሚዎች
- ለዕለት ሥራ የሚያስፈልጉ ሪፖርቶች
ምርታችን
ለአንድም ሆነ ለብዙ ቅርንጫፎች የተነደፈ የንግድ ማስተዳደሪያ ሥርዓት። ሽያጭ፣ ክምችት፣ ደንበኞች፣ ሠራተኞችና ገንዘብ በአንድ ቦታ — በካውንተር ላይም ሆነ ከቤት ሆኖ ሲሠሩ ሁልጊዜ ትክክለኛና አንድ አይነት መረጃ ያገኛሉ።

በቮርቴክስ ውስጥ
የአንድ የተዋሃደ ሥርዓት አሥር ክፍሎች። እያንዳንዱ ክፍል በራሱ ሙሉ ሲሆን፣ ተጨማሪ ሶፍትዌር አያስፈልገውም።
በካውንተር ወይም በስልክ ይሽጡ። እያንዳንዱ ሽያጭ በቀጥታ ወደአንድ ማዕከላዊ መዝገብ ይገባል።
የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር ይያዙ፤ የቅርንጫፎችን ክምችት ይከታተሉ፤ እቃ ከማለቁ በፊት አስቀድመው ማሳሰቢያ ያግኙ።
በቅርንጫፎች መካከል ዕቃዎችን ያዘዋውሩ፤ አሁን እያንዳንዱ እቃ የት እንዳለ በግልጽ ይመልከቱ።
ማን ምን እንደሚገዛ፣ ስንት ጊዜ እንደገዛ፣ እና ምን ያህል ቀሪ ሂሳብ እንዳለበት ይከታተሉ።
የአቅራቢዎችን መረጃ፣ የገቡ እቃዎችን እና ለእነሱ የተከፈሉ ክፍያዎችን በአንድ ላይ ያስተዳድሩ።
በዱቤ የተሸጡ ዕቃዎችን በደንበኛ ስም ከቀሪ ሒሳብና ከቆይታ ጊዜያቸው ጋር በግልጽ ይቆጣጠሩ።
ወጪዎች ከገቢዎች ጋር በአንድ ቦታ ስለሚመዘገቡ የድርጅትዎን ትክክለኛ ንጹህ ትርፍ ያገኛሉ።
የሠራተኞች ደመወዝ ሲስተሙ አስቀድሞ ከመዘገበው የመገኘት መረጃ ጋር ተሰልቶ ይዘጋጃል።
የእያንዳንዱን ሠራተኛ የሥራ ሰዓት በቅርንጫፍ ደረጃ ያለ ምንም የወረቀት መዝገብ በዘመናዊ ሁኔታ ይከታተሉ።
የዛሬው ሽያጭ፣ የዚህ ወር ትርፍ፣ እና ገቢው ከየት እንደመጣ አጠቃላይ ማጠቃለያ ያግኙ።
ቅርንጫፍ ተጨማሪ አማራጭ አይደለም። ክምችት፣ ዝውውር፣ ሠራተኛና ሪፖርት ሁሉ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ ከከፈቱበት ቀን ጀምሮ የየትኛው እንደሆኑ ያውቃሉ።
ሥራ አስኪያጅ፣ ካሽየርና የክምችት ኃላፊ የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ያገኛሉ። ባለቤቱ ግን ከየትም ሆኖ ሁሉንም ያያል።
ኢንተርኔት ሲቋረጥ ምን እንደሚሠራና ምን እንደማይሠራ ከመግዛትዎ በፊት በግልጽ እንነግርዎታለን — ከገዙ በኋላ አይደለም።
በመጨረሻ የተለጠፈ ትርጉም አይደለም። ካሽየርዎ በሚያስብበት ቋንቋ ይሠራል፤ እርስዎም እንዲሁ።
የቮርቴክስ ዕቅዶች
አራት ዕቅዶች፣ በወር። የማስጀመሪያ ሥራ አንድ ጊዜ ተተምኖ ሁሌም በስምምነቱ ውስጥ ይካተታል።
ከደብተር ላለፈ አንድ ሱቅ
እንነጋገር
ሁለተኛ ቅርንጫፍ ለሚከፍት ሱቅ
እንነጋገር
ሠራተኛ ላላቸው ብዙ ቅርንጫፍ ሱቆች
እንነጋገር
ትልልቅ ሥራዎችና ልዩ ፍላጎቶች
እንነጋገር
ዋጋዎች ሥራ ከመጀመሩ በፊት፣ ምን እንደሚካተትና ምን እንደማይካተት ጋር በጽሑፍ ይረጋገጣሉ።
ንግድዎ ምን እንደሚሠራና የት ላይ እንደሚዘገይ ይንገሩን። እኛ የምንስማማ መሆናችንን ለማወቅ አንድ ውይይት ብዙውን ጊዜ በቂ ነው — ካልሆንም በግልጽ እንነግርዎታለን።
hello@nanolinkstech.com